መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ቀ-ቁልዔ

    ቍልዕውና = ልጅነት ፤ ቁልዔ = ልጅ
  • ቀ-ቂቁይ

    ንፉግ (ኢይሁብ ቂቁይ ንዋየ ለሰብእ/ንፉግ ለስው ገንዘብ አይሰጥም)
  • ቀሠመ

    ለቀመ ፤ ቆረጠ ፡ ሰበሰበ
  • ቀሰመ

    አጣፈጠ ፤ ቀመመ ፤ አዋሐደ ፤ መጠነ አሟረተ ፡ ጠነቆለ
  • በ-ቢጽ

    እሉ አብያፅየ ውእቶሙ (እነዚህ ጓደኞቼ ናቸው)
  • በ-ባሕቱ

    እንጅ ፤ ነገር ግን ፤ ብቻ ባሕቲት-ብቻ ፣ ባሕቲቶሙ-ብቻቸውን ፤ ባሕቲትየ-ብቻየን ፤ ባሐቲታ-ብቻዋን ፤ እያለ ይቀጥላል በ፲ መራሕያን (ባሕቲትየ ነበርኩ ነዋኅ ሰዓት ፤ ባሕቱ አንተ መጻእከ ሊተ / አንተ መጣህልኝ እንጅ ረጅም ሰዓት ብቻየን ነበርኩ)
  • በ-ባረየ

    አፈራረቀ ተባረየ፤ ተፈራረቀ ዕብሬት-ተራ (ንበሪ አንቲ በዕብሬትኪ/አንቺ በተራሽ ተቀመጭ)
  • በ-ቤለ

    ተናገረ ፤ አለ
  • በ-ብሕትና

    ብቸኝነት
  • በ-ብዕል

    ብልጥግና፡ ባለጠግነት፡ ክብር
  • በ-ቦ

    አለ ፤ ነበረ ፤ ኖረ (እስመ አልብነ ረዳኢ/ረደት የለንም) ቦኑ (ጥያቄ ይሆናል)፦ አለነ? ነበረን? ቦኑ፦ በውኑ ፤ በእውነት (ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለእጓለ እመሕያው/ በውኑ ስውን በከንቱ ፈጠርከው) ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ/የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ፤ ቦ ዘወድቀ ውስተ ኩኵሕ/በአለት ላይ የወደቀ አለ/ነበር ፤ አንተ ውእቱ ዘብከ ሥልጣን/ሥልጣን ያለህ አንተ ነህ ሲዘረዘር፡ ብነ | ብከ | ብየ | ብኪ | ቦቱ | ባቲ | ብክሙ | ብክም | ቦሙ | ብን
  • በሊሕ

    የተሳለ ፤ ፈጣን
  • በቈዐ

    በቃ ተገባ ጠቀመ ረባ (የዐርጉ ወይወርዱ መስተገብራን ለበቈዔተ ሕዝብ/ገበሬዎች ለሕዝብ ጥቅም ይወርዳሉ ይወጣሉ)
  • በአሰ

    ጠላ ፤ ናቀ ተባአሰ፦ ተጣላ ፤ ተናናቀ (ዝ መጽሐፍ ይጸሐፍ ለአማስኖ ሰብእ/ ይህ መጽሐፍ ሰው ለማጣላት ነው ይተጻፈው)
  • በዐደ

    ለየ ፤ ነጠለ ፤ አገለለ ፤ ባዕድ አደረገ ፤ ልዩ አደረገ ብዑድ (የተለየ)
  • በይነ

    ስለ (ምንት ጸላእከኒ እኁየ? / ስለምን ጠላኸኝ ወንድሜ)
  • በደረ

    =›ሮጠ ፤ ፈጠነ ፤ ቀደመ ፤ ተወዳደረ =›አበደረ =› መረጠ ፤ ወደደ ፤ አከበረ (ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት / ከመሥዋዕትም ምጽዋትን እወዳለሁ አላቸው)
  • በጽሐ

    ደረሰ ፤ መጣ ፤ ደረሰ ፤ ቀረበ ፤ አደገ (በጽሐ ዓውደ አመት)
  • ተለወ

    ተከተለ ፤ መሰለ ፤ ወደደ። ተራ ያዘ ፤ አጀበ
  • ተሐየየ

    ቸል አለ
Previous Next