በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል (ሖ) ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።
-
ሀ-ህየ
ህየ= እዚያ ዝየ= እዚህ እምዝየ =ከዚህ እምህየ= ከዚያ እንተ ህየ = በዚያ በኩል እንተ ዝየ = በዚህ በኩል (ወያጸሉ ፡ ህየ ፡ አዕዋፈ ፡ ሰማይ) -
ሀለወ
አለ ፤ ኖረ (እስመ ከመዝ ሀለዎ ይኩን/ይህ ይደረግ ዘንድ አለውና) -
ሀበ
ሀበ፦ ትርጉም ሰጠ (ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ወሀበ ሕይወት / ከርስቶስ ከሙታን ተነሳ ሕይወትንም ሰጠ) -
ለ-ሊተ
ለኔ ፤ እኔ ፤ እኔን ፤ ወደኔ ፤ -ልኝ(ብእሲት እንተ ጸሐፈት ሊተ ጦማረ/ደብዳቤ የጻፈችልኝ ሴት ፤ ዝ ቤት ሊተ ውእቱ ዘወሀበኒ አቡየ/ይህ ቤት አባቴ የሰጠኝ ነው ፤ ስምዑኒ ሊተ/እኔን ስሙኝ)። በ፲ መራሕያን፦ ሊተ/ለነ/ለከ/ለኪ/ለክሙ/ለክን/ሎቱ/ላቲ/ሎሙ/ሎን -
ለሐመ
ጸና፣ በረታ፣ ከፋ -
ለምንት
ለምንት - ለምን ምንት - ምን -
ለበወ
ልብ አደረገ አስተዋለ ዐወቀ ኢለበውኩ=አልገባኝም -
ለፌ ወለፌ
ወዲህ ወዲያ (ኢትበሉ ለፌ ወለፌ) -
ሐ-ሖረ
ሖረ ትርጉም ፦ ሄደ (ኢየሱስ ሆረ እምገሊላ ሀበ ዩሀንስ / ኢየሱስ ከገሊላ ወደ ዮሀንስ ሄደ) ኀበ=ወደ -
ሐለመ
አለመ -
ሐለየ
አሰበ ፤ ገመተ ፤ መረመረ -
ሐመ
ታመመ -
ሐመለ
ለቀመ ፤ ለመለመ -
ሐመመ
ተመቀኘ -
ሐሰወ
ዋሸ (አመንየ ውእቱ ወአኮ ሕሳዌየ/እውነቴን ነው ውሸቴን አይደለም) -
መ-ሙቃስ
ወቀሳ -
መ-ሚ
ማ ፤ ማን ፤ ምን ፤ ምንኛ ፤ ምን ያህል (ሚ የዐቢ አምላⷈ/አምላኬ ከአንተ ማን ይበልጣል ፤ ሚ ትሤኒ እንተ ወለደታ ሐና/ ሐና የወለደቻት ምን(ኛ) ታምር -
መ-ምስለ
ጋር አብሮ (ይመጽእ እግዚእ ፡ ምስለ መላእክቲሁ/ጌታ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል) -
መ-ምዕረ
አንድ ጊዜ (ምዕረ በዘባነኪ ወምዕረ በገቦኪ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕጻን ደከምኪ) -
መሠጠ
ነጠቀ ፤ አምሠጠ(አመለጠ) ፤ መሣጢ (ዘራፊ)