ከግእዝ ቤተሰብ ዌብሳይታችን ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ከዚህ በታች አቅርበናል። የእርስዎ ጥያቄ ከዚህ በታች ካሉት ጥያቄዎች ውጭ ከሆነ ይጻፉልን። እዚህ ይጫኑ
- Website
- ስለ ግእዝ ቤተሰብ
- Facebook
- አጠቃላይ
ወደፊት የምማራቸውን ትምህርቶች መክፈት አልቻልኩም
የእለቱን ትምህርት ሳይጨርሱ ወደሚቀጥለው ትምህርት መሄድ ወይም የወደፊት ትምህርቶችን መክፈት አይችሉም።
የእለቱን ትምህርት ጨርሼ ወደሚቀጥለው እለት ትምህርት መሄድ ብፈልግ ከየት ነው የማገኘው?
የአንድ እለት ትምህርት ከፍተው የሚማሩበት page ላይ በቀኝ በኩል የትምህርቱ ማውጫ ይገኛል። የእለቱን ትምህርት ከጨረሱ ፤ የሚቀጥለውን እለት ለመማር የትምህርቱ ርእስ ላይ ይጫኑ። የእለቱን ትምህርት ሳይጨርሱ ወደሚቀጥለው ትምህርት መሄድ አይችሉም።
እየተማርኳቸው ያሉትን ትምህርቶች የት አገኛቸዋለሁ፧
ከላይ My Courses የሚለውን ተጭነው ከሚቀጥለው page ላይ COURSES የሚለውን ሲጫኑ እየተማሩ ያሉትን ትምህርቶች በአንድ ቦታ ያገኙአቸዋል። (My Courses > Courses)
እንዴት ከሌሎች ጋር በመረዳዳት መማማር ይቻላል?
ቋንቋ በመለማመድ የሚያዳብሩት ክሂሎት እንጂ እያጠኑ የሚያውቁት እውቀት ብቻ አይደለም። በግእዝ ቤተሰብም ተማሪዎች እየተረዳዱ ፤ የተማሩትን በጋራ እየተለማመዱ ግእዝ ቋንቋን እንዲማሩ ይበረታታል። በግል ከመማር ይልቅ ከቤተሰብ ፤ ከጓደኛዎ ፤ ከስራ ባልደረባዎ ፤ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ቢማሩ የበለጠ ውጤታማ መሆን ይቻላል። በግእዝ ቤተሰብ ተማሪዎች በቡድን እንዲማሩ ይመቻቻል። በተጨማሪም ፌስቡክ group ላይ ጥያቄ በመጠየቅ እና መልስ በመመለስ መሳተፍ ይቻላል። ተጨማሪ እገዛ ከፈለጉ Contact Us የሚለውን ተጭነው ይጻፉልን።
ይህንን ዌብሳይት እንዴት እጠቀምበታለሁ?
ይህንን ዌብ ሳይት ተጠቅመው ግእዝ ለመማር ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለማወቅ እዚህ ይጫኑ
geezFamily.com ማን ነው የሚማርበት፧
GeezFamily.com ዘር ፤ ቀለም ፤ ቋንቋ ፤ ወንዝ ፤ ጾታ ፤ እድሜ ሳይለይ ግእዝ ቋንቋን መማር የሚፈልግ ሰው ሁሉ የሚማርበት መድረክ ነው።
geezFamily.com ማን ነው የሚያስተምርበት?
ይህ ዌብሳይት ተማሪዎች የግእዝ ቋንቋ የሚማማሩበት ፤ ፈቃደኛ መምህራን ቋንቋውን የሚያስተምሩበት ፤ ሌሎች አቅም ያላቸው ደግሞ ተማሪዎችን የሚረዱበት የጋራ መድረክ ነው። የዚህ ዌብሳይት በር ለሁሉም ክፍት ነው።
የ geezFamily.com ዓላማ ምንድን ነው?
የግእዝ ትምህርት እንዲስፋፋ ማገዝ እና ለትንሳኤ ግእዝ የአቅማችንን ማበርከት ነው።
Facebook ላይ ምን አይነት መረጃ ማስተላለፍ ይቻላል?
በ Facebook ግሩፕ ውስጥ geezFamily.com ከተመሰረተለት አላማ ውጭ ሌላ ፖለቲካ ፤ የዘረኝነት ፤ የግል እንዲሁም ማንኛውንም ተመሳሳይ መረጃ መለጠፍ ክልክል ነው።
Facebook group እንዴት እገባለሁ
Facebook group ለግእዝ ተማሪዎች ብቻ ክፍት ስለሆነ ተማሪ ሆነው ግሩፑ ውስጥ ካልገቡ እዚህ ይጫኑ።
ግእዝ ለመማር ካህን መሆን ይጠበቅብኛል?
ግእዝ እንደ መግባቢያ ቋንቋ ለመማር ክህነት አያስፈልግም ፤ ጾታ ፡ እድሜ ፡ ዘር ፡ ወዘተ አይለይም። ግእዝ የሁሉም ቋንቋ ነው።