Courses

በርካታ የታሪክ እና የስነ ልሳን ተመራማሪዎች ስለ ግእዝ ቀዳሚነት እና ምስጢራዊነት ብዙ ጽፈዋል። ግእዝ እንደ ማንኛውም ቋንቋ የራሱ የሆነ የአጻጻፍ ሥልትና ቅርጽ የተከተለ ጥንታዊ ቋንቋ ነው። ይህ የትንቢት የምርምር እና የጸሎት መሳርያ የሆነ ውብ ቋንቋ ኅልውናው እንዲጠበቅ ፤ እንዲያድግና እንደ ማንኛውም ቋንቋ ወደ መነጋገርያ ቋንቋነት እንዲመለስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርሻ ነው።

በዚህም መሰረት geezFamily.com የቋንቋው ባለሞያዎች እና ተማሪዎች የሚማማሩበት መድረክ ነው። በዚህ ድኅረ ገጽ ላይ ከዚህ በታች ካሉት ትምህርቶች በተጨማሪ በርካታ የግእዝ ትምህርት አይነቶች ወጣቱ ትውልድ ሊረዳ በሚችለው ዘመናዊ አቀራረብ በተለያዩ ምሁራን እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን እግዚአብሄር ቢረዳን በርካታ ስራዎችን ለመስራት አቅደናልና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወንዝ ፤ ዘር ፤ ፖለቲካ ሳይገድበው ቋንቋውን እንዲማር ፤ የሞያው ባለቤቶች ደግሞ ያላችሁን ችሎታና እውቀት ለትውልዱ በማካፈል የትውልድ ግዴታችሁን እንድትወጡ geezFamily.com ድኅረ ገጽን እነሆ ብለናል። ይማሩ!!!


የግእዝ ቋንቋ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ - ቀዳማይ

ይህ ትምህርት ግእዝን እንደ ቁንቋ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን ግእዝ ጀማሪዎች ለሆኑ መሰረታዊ ዕውቀቶችን እንዲያገኙ እና ለቀጣይ ትምህርት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የታሰበ ነው። ማንኛውንም ችሎታ ለማዳበር መለማመድ /practice/ ትልቁን ቦታ እንደሚይዝ የታወቀ ነው። ስለሆነም ተማሪዎች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የቴሌግራም መለማመጃ መርኃ ግብሮችን እናዘጋጃለን።...Read More
ግእዝ ሰዋስው - ቀዳማይ

የግእዝ ቋንቋ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ - ካልዓይ

ይህ ትምህርት ተማሪዎች በግእዝ ቋንቋ አረፍተ ነገሮችን እንዲመሰርቱ የሚያስችል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ግእዝን እንደ መግባቢያ ቋንቋ ለመማር ተማሪዎች በቪድዮ የተማሩትን ከሌሎች ተማሪዎች እና መምህሩ ጋር ቢለማመዱ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማምጣት ይቻላል። በዚህም መሰረት በዚህ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ተማሪዎች እየተጠባበቁ...Read More

14 thoughts on “Courses

    1. Thank you for visiting the site. We are really working hard to get something out there for “ትንሳኤ ግእዝ”. Keep your eye. We will let you know when upcoming courses are live.

      1. Really I am thankful for having such a wonderful family!!! Also I want to thanks Rahel for her kind support in registering me!!
        እግዚአብሔር ይመስገን እናንተን የመሰለ ቤተሰብ ለሰጠኝ !!! እራሄልን ስለ ቀና ትብብሯ በምዝገባ ስህተት እያለ አልቀበል ሲለኝ ረድታኛለች እግዚአብሔር እድሜና ጤናን ይስጥልኝ

  1. ቡራኬዎ ይድረሰን አባታችን እግዚአብሔር ይስጥልን የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለፅልን በፀሎት አስቡን!

  2. እግዚአብሔር ይሀብልነ ለመምህራንነ ለዘአስተዳልወልነ
    እግዚአብሔር ያስፈጽመነ በትጋህ

Leave a Reply