በአሁኑ ጊዜ ወጣቱ ትውልድ ከምንጊዜውም በበለጠ የግእዝ ቋንቋ ለመማር የተነሳሳበት ነው። ሊቃውንቱም ከመደበኛው የአብነት ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ ዘመኑ ባፈራቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም በተለያዩ መንገዶች (በማኅበራዊ ሚዲያ ፤ በድኅረ ገጽ ፤ በመጽሀፍ…) ያስተምራሉ። የግእዝ ቤተሰብ ዌብሳይትም ይህንን ጥረት ለመደገፍና ቋንቋውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን ለመወጣት የተዘጋጀ ነው። ይልቁንም ይህ ዌብሳይት የቋንቋው ባለሞያዎች እና ተማሪዎች ተገናኝተው የሚማማሩበት መድረክ ለመፍጠር ዘርና የፖለቲካ አመላካከት ሳይለይ ቋንቋውን ለሁሉም ለማዳረስ የተዘጋጀ ነው።
እርስዎም ግእዝን በመማርም ሆነ በማስተማር ለቋንቋው ትንሳኤ እና እድገት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ።