ይህ ትምህርት ግእዝን እንደ ቁንቋ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን ግእዝ ጀማሪዎች ለሆኑ መሰረታዊ ዕውቀቶችን እንዲያገኙ እና ለቀጣይ ትምህርት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የታሰበ ነው።
ማንኛውንም ችሎታ ለማዳበር መለማመድ /practice/ ትልቁን ቦታ እንደሚይዝ የታወቀ ነው። ስለሆነም ተማሪዎች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የቴሌግራም መለማመጃ መርኃ ግብሮችን እናዘጋጃለን። ተማሪዎችም በመርኃ ግብሮቹ ላይ እየተሳተፉ ከቪድዮ የተማሩትን እንዲለማመዱ ይጠበቃል።
ይህ ትምህርት በቪድዮ የተዘጋጀ ሲሆን በበቂ ምሳሌዎችና መልመጃዎች የተደገፈ ነው። ከዚሀ በተጨማሪ ተማሪዎች አዳዲስ ቃላት እንዲያጠኑና በአጭር ጊዜ የግእዝ ቋንቋ ዕውቀታቸውን እንዲያሳድጉ በየዕለቱ የሚያጠኗቸው ቃላት (Vocabularies) ተለይተው ቀርበዋል።
ቀጣይ ዙር/batch/ ምዝገባ ማስታወቂያ በቴሌግራም እንለጥፋለን ይከታተሉን። ግሩፑን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
Module 1 | መግቢያ |
ትምህርት 1 | መግቢያ |
ትምህርት 2 | ፊደላት |
Module 2 | መሠረታዊ ቃላት |
ትምህርት 1 | ጊዜን ለመግለጽ የሚጠቅሙ ቃላት |
ትምህርት 2 | መጠይቅ ቃላት |
ትምህርት 3 | ቦታን ለመግለጽ የሚጠቅሙ ቃላት |
Module 3 | መራሕያን |
ትምህርት 1 | መራሕያን |
Module 4 | ተናባቢ ቃላት/ሐረጋት |
ትምህርት 1 | ተናባቢ ቃላት/ሐረጋት |
Module 5 | አኃዝ |
ትምህርት 1 | አኃዝ |
Module 6 | ክፍላተ አካል |
ትምህርት 1 | ክፍላተ አካል |
Module 7 | ሰብአ ቤት |
ትምህርት 1 | ሰብአ ቤት |
Module 8 | ጠቃሚ ፊደላት |
ትምህርት 1 | ጠቃሚ ፊደላት - ክፍል ፩ |
ትምህርት 2 | ጠቃሚ ቃላት - ክፍል ፪ |
ትምህርት 3 | ጠቃሚ ቃላት - ክፍል ፫ |