በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል (ሖ) ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።
-
መነነ
ናቀ (ምኑን ዮሴፍ ትሠመ / የተናቀ ዮሴፍ ተሾመ) -
መኑ
ማን - እለ መኑ አንትሙ (እነ ማን ናችሁ) መኑመ - ማን ይሆን?! -
መንገለ
ወደ/towards -
መከረ
፩. መከር ፪. ሞከረ -
መጽንሕ
መቆያ -
መጽአ
ትርጉም፡ መጣ ዐረፍተ ነገር፡ አቡየ መጽአ እምሐገሮሙ (አባቴ ከሐገሩ መጣ) ልብ በል፡ አቡየ ማለት አባቴ ማለት ነው። “እም” ማለት “ከ” ማለት ነው - ከሐገሩ እንደማለት -
ሠ-ሤመ
ሾመ ፤ ሸለመ ፤ አሠልጠነ ፤ አከበረ -
ሠ-ሤጠ
ሸጠ ፤ ለወጠ ፤ ሰጠ ተቀበለ -
ሠረቀ
ወጣ ፤ ታየ ፤ በራ ፤ ተገለጠ ሠርቅ (መውጫ) -
ረ-ርእየ
አየ ፤ ተመለከተ (ርኢኩ ያሬድሃ/እኔ ያሬድን አየሁት) -
ረሰየ
አደረገ ፡ ሰራ (በቃና ዘገሊላ ማየ ረሰየ ወይነ / በገሊላ ቃና ውኃውን ወይን አደረገው) -
ረዐየ
ጠበቀ ፤ አሰማራ ፤ ነዳ ፤ ተከተለ -
ረፈቀ
ተቀመጠ = (ረፈቀ መልዕልተ አራት/አልጋ ላይ ተቀመጠ) -
ሰ-ስእነ
ደከመ ፤ ታከተ -
ሰ-ስዕነ
አቃተ፤ተሳነ (አርዳኢሁ ይቤልዎ ለእግዚአ ኢየሱስ በእንተ ምንት ንሕነ ስዕነ አውፅኦቶ/ሐዋርያቱም ጌታችን ኢየሱስን እንዲህ አሉት "ስለምን እኛ ማስወጣት ተሳነን") -
ሰ-ሶበ
ጊዜ (ሶበ ይመጽእ/በሚመጣበት ጊዜ) -
ሰረቀ
ወሰደ ፤ አጠፋ ፤ አበላሸ -
ሰንአ
ገጠመ ፤ ለካ ፤ አስማማ (ተሰነአውክሙኑ ንዛዋዕ በእንተ ቤተ ክርስቲያን?) -
ሰከየ
ከሰሰ -
ሰወጠ
ተለወጠ