መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ገ-ጋብአ

    ሰበሰበ ፤ አከማቸ (ዖፍ እንተ ታስተጋብእ እጎሊሃ/ልጆችዋን የምትሰበስብ ወፍ)
  • ገ-ጌሠ

    ትርጉም፦ ገሰገሰ ፤ ሄደ ፤ ዘመተ
    ምሳሌ፦ጌሥኩ አነ ኀበ አራት ኪሎ። (ወደ አራት ኪሎ ሂድኩ)
  • ገ-ጐንደየ

    ዘገየ (ለምንት ጐንደይከ እኁነ?/ወንድማችን ለምን ዘገየህ)
  • ገልበበ

    ሸፈነ ከደነ (ዘይገለብብቦ ለሰማይ በደመና/ሰማይን በደመና የሚሸፍን)
  • ገሐሰ

    ገባ ፤ ፈለሰ ፤ አደረ ፤ ተጓዘ (ተግሕሰት ፍኖታ እንዘ ታስተጥዕም ውእተ ወይን/ወይኑን እያጣጣመች መንገዷን ቀጠለች/ተጓዘች)
  • ገብረ

    ሠራ (መንክር ግብር ዘተገብረ ተከሰተ/የተሠራው አስደናቂ ሥራ ተገለጠ)
  • ጠ-ጥቀ

    ትርጉም፦ እጅግ ፤ ለካ ፤ ፈጽሞ ፤ ይልቅ ፤ በጣም
  • ጠ-ጥይቅና

    ጥይቅና = ትክክለኝነት (exactness) ጥዩቀ/በጥይቅና = በትክክል (exactly)
  • ጸ-ጽጌ

    ጽጌ ማለት = አበባ - ንሕብ ቀሠመት ጽጌ (ንቧ አበባ ቀሠመች)
  • ጸሐበ

    ሰለቸ ፤ ዘበዘበ
  • ጸብአ

    ጸብአ - ተጣላ፤ ተዋጋ ጸባኢ - የሚጣላ ፤ ወታደር ጸባኢት - አሸናፊ ጸብእ - ጥል ፤ ጦርነት ጽቡእ - የተሸነፈ ፤ የተወጋ ቁስለኛ (ኢንፃባህ/አንጣላ) ጸብዐ ማለት ግን ቀሰረ ማለት ነው
  • ጸነሰ

    ተቸገረ ፤ አጣ (እሴብሐከ አልቦ ተጽናስ / አመሰግናለሁ ችግር የለም)
  • ጸንሐ

    ቆየ ፤ ደጅ ጠና ፤ ታገሰ (ጽንሑ በሰላም)
  • ጸዋግ

    ክፉ ፤ መጥፎ ፤ ጨካኝ (ኮረና ደዌ ፀዋግ ውእቱ)
  • ጸውአ

    ጠራ (ዮሐንስሃ ጸውአ ታዴዎስ/ታዴዎስ (ዮሐንስን ጠራ)
  • ጸውዐ

    ሰጠ (ፍንው ጴጥሮስ ዘተጸውዐ ጸሐፈ መልእክተ/የተጠራው የተላከ ጴጥሮስ መልእክት ጻፈ)
  • ጸዐቀ

    ተጨነቀ ፤ ተቸገረ (ለምንት ትጸዐቁ ኩልክሙ በእንተ ነገር ኢትክህሉ ባሕቶሙ)
  • ጸገወ

    ሰጠ ፤ ለገሰ
  • ፀ-ፆረ

    ተሸከመ
  • ፈለግ

    ወንዝ (ወረድከ አንተ ኀበ ፈለግ/አንተ ወደ ወንዝ ወረድህ)
Previous Next