ለመመዝገብ

በቴሌግራም ስልክ ቁጥርዎ ለመመዝገብ ከዚህ በታች ያለውን ይከተሉ፦

1ኛ፦ መመዝገቢያ ድኅረ ገጹን ይክፈቱ

በቴሌግራም ቁጥርዎ ለመመዝገብ መጀመርያ መመዝገቢያ ድኅረ ገጹን ከፍተው Login With Telegram የሚለውን ይጫኑ። ድኅረ ገጹን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

2ኛ፦ የስልክ ቁጥርዎን ያስገቡ

ከዚህ በታች በፎቶ ላይ እንደሚያዩት የቴሌግራም ስልክ ቁጥርዎን ያወጡበትን አገር መርጠው የስልክ ቁጥርዎን ያስገቡ። ከዚያም NEXT የሚለውን ይጫኑ።

3ኛ፦ ቴሌግራም ላይ Confirm የሚለውን ይጫኑ

ከላይ እንዳሳየነው NEXT የሚለውን ሲጫኑ ቴሌግራም መልእክት ይልክልዎታል። ስለዚህ ቴሌግራም ከፍተው የቴሌግራም መልእክቱን ከፍተው ከዚህ በታች እንዳለው ፎቶ Confirm የሚለውን ይጫኑ።

4ኛ፦ የመጨረሻ ማረጋገጫ

ከላይ እንዳሳየነው ቴሌግራም ላይ Confirm የሚለውን ከተጫኑ በኋላ ከላይ 2ኛ ላይ ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡበት ገጽ ላይ  ተመልሰው ከዚህ በታች እንዳለው ፎቶ Accept የሚለውን ይጫኑ።

ከዚህ በታች ካሉት ሁለት አማራጮች አንዱን ተጭነው በቀጣይነት ማድረግ ያለብዎትን ያሳይዎታል።

  • አስቸግሮኛል ወይም ርግጠኛ አይደለሁም
  • ከላይ ያለውን በትክክል ጨርሼ ተመዝግቤአለሁ

ከላይ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ድረስ ያሉትን መከተል ካስቸገረዎ ወይም ርግጠኛ ካልሆኑ እንዴት እንደሚመዘገቡ የሚያሳይ ቪድዮ አዘጋጅተናል እዚህ ተጭነው ይመልከቱ

ተመዝግበው ሲጨርሱ እዚህ ገጽ ላይ ተመልሰው "ከላይ ያለውን በትክክል ጨርሼ ተመዝግቤአለሁ" የሚለውን አማራጭ መምረጥ ይኖርብዎታል።

ከላይ ከ፩ኛ እስከ ፬ኛ ያሉትን ተከትለው ተመዝግበው ከሆነ ምዝገባ ጨርሰዋል ድኅረ ገጹ ላይ ያሉትን ቪድዮዎች ማግኘት ይችላሉ። ነገር ግን ለአዲስ ተመዝጋቢዎች አዲስ የመለማመጃ ቴሌግራም ግሩፕ አዘጋጅተናል ግሩፑ ውስጥ እንድናስገባዎት የቴሌግራምዎን User Name በውስጥ መስመር ይላኩልን።

የቴሌግራም User Name ፕሮፋይል ፎቶ የሚቀየርበት ቦታ ያገኙታል። እንዴት እንደሚያገኙት ካስቸገረዎ ቴሌግራም ላይ

Settings

Edit profile

ከዚያ User Name የሚል ያገኛሉ። User Name የሚለው ቦታ ላይ None የሚል ከሆነ የለዎትም ማለት ነው አዲስ User Name መፍጠር ይኖርብዎታል።

የተመዘገቡትን ትምህርት ቪድዮዎች እንዴት እንደሚያገኙ ለመረዳት እዝህ ተጭነው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።