በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል (ሖ) ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።
-
ፈለግ
ወንዝ (ወረድከ አንተ ኀበ ፈለግ/አንተ ወደ ወንዝ ወረድህ) -
ፈርሐ
ፈርሐ=ፈራ መፍርሕ=አስፈሪ መፍርሕት=አስፈሪ (እንስት) ፈራሕ=ፈሪ (ተባእት ፤ እንስት) (መፍርሕ ኮሮና አደንገፀ ብዙሓነ/አስፈሪ ኮሮና ብዙዎችን አስደነገጠ) -
ፈተነ
ሞከረ (ኦሆ እፈትን። አንተ ትረድአኒ/እሽ እሞክራለሁ አንተ ትረዳኛለህ) -
ፈተወ
ፈለገ (አነ ናሁ እፈቱ/እኔ አሁን እፈልጋለሁ) -
ፈትሐ
ፈታ ፤ ነጻ አደረገ ፍትሕ=ሕግ ፍትሐ ሞት=የሞት ፍርድ መፍትሕ = መፍትሄ -
ፈነወ
ትርጉም ፦ ላከ ፤ ሸኘ ፤ ለቀቀ ፤ አዘዘ (ፈነወ ለነ መዝራዕቶ ልዑለ / ልዑል ክንዱን ላከልን ) (የሰኞ ውዳሴ ማርያም ተፈሣህ) መዝራዕት=ክንድ -
ፈድፈደ
በዛ ፤ በለጠ (ትዕግስትኪ ፈድፈደ) -
ፈግዐ
ተደሰተ ፤ ደላው