መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ጸ-ጽጌ

    ጽጌ ማለት = አበባ - ንሕብ ቀሠመት ጽጌ (ንቧ አበባ ቀሠመች)
  • ጸሐበ

    ሰለቸ ፤ ዘበዘበ
  • ጸብአ

    ጸብአ - ተጣላ፤ ተዋጋ ጸባኢ - የሚጣላ ፤ ወታደር ጸባኢት - አሸናፊ ጸብእ - ጥል ፤ ጦርነት ጽቡእ - የተሸነፈ ፤ የተወጋ ቁስለኛ (ኢንፃባህ/አንጣላ) ጸብዐ ማለት ግን ቀሰረ ማለት ነው
  • ጸነሰ

    ተቸገረ ፤ አጣ (እሴብሐከ አልቦ ተጽናስ / አመሰግናለሁ ችግር የለም)
  • ጸንሐ

    ቆየ ፤ ደጅ ጠና ፤ ታገሰ (ጽንሑ በሰላም)
  • ጸዋግ

    ክፉ ፤ መጥፎ ፤ ጨካኝ (ኮረና ደዌ ፀዋግ ውእቱ)
  • ጸውአ

    ጠራ (ዮሐንስሃ ጸውአ ታዴዎስ/ታዴዎስ (ዮሐንስን ጠራ)
  • ጸውዐ

    ሰጠ (ፍንው ጴጥሮስ ዘተጸውዐ ጸሐፈ መልእክተ/የተጠራው የተላከ ጴጥሮስ መልእክት ጻፈ)
  • ጸዐቀ

    ተጨነቀ ፤ ተቸገረ (ለምንት ትጸዐቁ ኩልክሙ በእንተ ነገር ኢትክህሉ ባሕቶሙ)
  • ጸገወ

    ሰጠ ፤ ለገሰ