መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ደ-ዳእሙ

    እንጅ ፤ ግን ፤ ይልቅ (ኢትፍራህ ተአመን ዳእሙ / እመን እንጂ አትፍራ)
  • ደ-ድራር

    እራት
  • ደለወ

    መዘነ ፤ አስተካከለ ፤ አዘጋጀ (እም እንተ ታስተዴሉ ምግበ ለደቃቅ/ ለልጆችዋ ምግብ የምታዘጋጅ እናት)