መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ዘ-ዚአከ

    አገናዛቢ ስሞች=Possessive pronouns ዚአየ=የኔ/Mine ዚአነ=የኛ/Ours ዚአከ=ያንተ/Yours ዚአክሙ=የናንተ/Yours ዚአኪ=ያንቺ/Yours ዚአክሙ=የናንተ/Yours ዚአሁ=የሱ/His ዚአሆሙ=የነሱ/Theirs ዚአሃ=የሷ/Hers ዚአሆን=የነሱ/Theirs (ዘዚአነ ሞተ ነስአ ወእንቲአሁ ሕይወተ ወሀበነ/የኛን ሞት ነሳ የእርሱን ሕይወት ሰጠን)
  • ዘ-ዝንቱ

    ይህ - ዝንቱ ውእቱ ዘመዱ ለአብርሃም (ይህ የአብርሃም ዘመድ ነው)...ተጨማሪ
  • ዘ-ዝየ

    ዝየ= እዚህ ህየ= እዚያ እምዝየ =ከዚህ እምህየ= ከዚያ እንተ ህየ = በዚያ በኩል እንተ ዝየ = በዚህ በኩል ምንተ ንገብር ዝየ / እዚህ ምን እንሠራለን?
  • ዘሐቀ

    ዛቀ ፤ አፈሰ ቀረፈ ፤ ላጠ
  • ዘረወ

    በተነ - ነፋስ ዘረወ ደመና (ነፋስ ደመናውን በተነ)
  • ዘበጠ

    መታ - ካህን ዘበጠ ከበሮ (ካህን ከበሮ መታ)
  • ዘንግዐ

    ዘነጋ ፤ ረሳ