በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል (ሖ) ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።
-
ወ-ውእተ አሚረ
ያን ጊዜ (እስመ ለነ ለኃጥኣን ለእመ መሐርከነ ውእተ አሚረ ትሰመይ መሓሬ ወለጻድቃንሰ እምግባሮሙ ትምሕሮሙ ወትዔስዮሙ በከመ ጽድቆሙ / እኛን ኃጥኣንን ብትምረን ያንጊዜ መሓሪ ትባላለህ ጻድቃንን ግን ከስራቸው የተነሳ ትምራቸዋለህ እንደ ጽድቃቸውም ትከፍላቸዋለህ፡፡(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)) -
ወ-ውእቱ
ውእቱ ማለት = ነው ፧ ናት ፧ ነህ ፧ ነሽ ፧ ናቸው ፧ ናችሁ ፧ ነን ፧ ነበረ ፧ ነበረች ፧ ነበርህ ፧ ነበርሽ ፧ ነበርሁ ፧ ነበሩ ፧ ነበራችሁ ፧ ነበርን -
ወለት
ሴት [ልጅ] -
ወሐየ
ጎበኘ ፤ ጠየቀ -
ወይ
ወየው ፤ ዋይ ፤ ውይ (ወይ ሊተ / ወዮልኝ) -
ወገበ
ድንገት መጣ ፤ ወጀበ ፤ አኮረፈ (ሞተ ግብት/ድንገተኛ ሞት) -
ወጠነ
ጀመረ