መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ከ-ኮነነ

    ገዛ
  • ከ-ኵናት

    ማለት፦ ጦር ፤ ዘገር ፤ መውጊያ ፤ አንካሴ
    ምሳሌ፦አዝማዲነ ኀልቁ በኤድስ ወበኵናት (ዘመዶቻችን በኤድስ እና በጦርነት አለቁ)
  • ከልአ

    ንከልአ -ሁለት አደረገ ካልእ - ሁለተኛ ፤ ሌላ ፤ ጓደኛ (ካልአን/ት/እት) (ተአሰረ ዳንኤል ወካልአኒሁ ከማሁ/ዳንኤል ታሰረ ፤ ሌሎቹም እንደሱ ታሰሩ) -ወካልእታኒ [አስቴር] ተአስረት/ሌላኛዋም ታሰረች። -ኀደገ ዮሴፍ ብሔሮ ወሖረ ኀበ ካልእ ብሔር /ዮሴፍ አገሩን ተወና ወደ ሌላ አገር ሄደ።
  • ከልዐ

    አወለቀ ፤ ከላ
  • ከተመ

    ከተመ ፤ ዘጋ ፤ አሸገ ከተማ (ጫፍ ፤ ራስ ፤ ዳርቻ)