መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • አ-እለ

    እነ - (እለ መኑ አንትሙ/እናንተ እነ ማን ናችሁ ፤ እሉ እሙንቱ እለ ይትሜክሁ በተግባሮሙ/በስራቸው የሚመኩ እነዚህ ናቸው)
  • አ-እመ

    በ ፤ ባ ፤ ቢ ፤ ብ፤ ከ ፤ ካ ፤ ምናልባት (እመ እግዚአብሔር ኢዐቀበ ሀገረ..../እግዚአብሔር ከተማን ልጠበቀ ...)
  • አ-እስኩ

    እስኩ - እስኪ (እስኩ ንርአይ ዘያድኅነክሙ ዮም/ ዛሬ የሚያድናችሁን እስኪ ዛሬ እናያለን ፤ ንግርኒ፡ እስኩ/ንገሪኝ)
  • አ-እስፍንቱ

    ስንት/ምን ያህል
  • አ-እንከ

    እንግዲህ (መኑ እንከ ጠቢብ / እንግዲህ ጠቢብ ማነው) ተገበሩ እንከሰ አኮ ለመብልዕ ኃላፊ፤አላ ለመብልዕ ዘይነብር ለህይወት ዘለዓለም ዘይሁብክሙ ወልደ እጓለእመሕያው
  • አ-እወ

    እውነት ፤ በእውነት
  • አ-እፎ

    እንዴት (እፎ ኀደርከ / እንዴት አደርህ)
  • አ-ኦሆ

    ትርጉም፦ እሺ ፤ ይሁን ፤ በጀ (በልኒ ኦሆ / እሺ በይኝ)
  • አሌ

    ወዮ (አሌ ለኪ/ ወዮልሽ)
  • አመነየ

    አስጐመዠ | አስመኘ
  • አማሰነ

    አጠፋ (ምንት አማሰንኩ?/ምን አጠፋሁ?)
  • አምጣነ

    ያህል ፣ ና ፣ ስለ (ኖመ ወልድየ አምጣነ ደክመ/ልጄ ስለደከመው ተኛ)
  • አኮ ባሕቲቱ… አዲ

    ብቻ ሳይሆን... ም (አኮ ባሕቲቱ ዓዲ እሙኒ/እሱ ብቻ ሳይሆን እናቱም) Not only...but also...
  • አውስአ

    መለሰ ፤ ተናገረ ፤ መልስ ሰጠ አውሳኢ(መላሽ ፤ መልስ ሰጭ) ፤ ተዋስኦ (ምልልስ ፤ ውይይት) ፤ አስተዋስአ (አነጋገረ) ፤ አውስ (መልስ)
  • አዛል

    አደገ ፤ በረታ ፤ ጎለመሰ ፤ ታላቅ (አንቲ አዛል እም ኩሎን አርድእት)
  • አይቴ

    የት፤ወዴት - አይቴ ሖርከ አንተ (አንተ ወደየት ሄድህ)
  • አደም

    አማረ (አዳም ውእቱ ላህየ ገጽከ/መልክህ የሚያምር ነው። ይኤድም አዕይንቲከ/አይኖችህ ያምራሉ)