መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ነ-ኖመ

    ትርጉም፡ ተኛ ምሳሌ፦ኖምከ አንተ ላዕለ አራት (አንተ አልጋ ላይ ተኛህ)
  • ነበረ (ላልቶ ይነበባል)

    ትርጉም፦ ተቀመጠ
  • ነጸረ

    ትርጉም ፡- ተመለከተ ፤አስተዋለ ፤ አተኮረ (ነጸረ አብ እምሰማያት / እግዚአብሄር አብ ከሰማያት ተመለከተ)
  • ነፍጸ

    ሸሸ ፤ አመለጠ (ወበግዕ ፡ ዘድኅነ ፡ እምነ ፡ አዝእብት ፡ ነፍጸ ፡ ወኀለፈ ፡ ውስተ ፡ አዕዱገ ፡ ገዳም) አዝእብት-ጅቦች አእዱግ-አህዮች