መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ተለወ

    ተከተለ ፤ መሰለ ፤ ወደደ። ተራ ያዘ ፤ አጀበ
  • ተሐየየ

    ቸል አለ
  • ተሐየየ

    ቸል አለ
  • ተሳምዐ

    ተስማማ ተደማመጠ
  • ተባሀለ

    ተከራከረ
  • ተናበበ

    ተናገረ (ሶበ ተናበበ / በተናገረ ጊዜ)
  • ተወክፈ

    ትርጉም፡፡ተቀበለ (ተወከፍ መባኦሙ ለአኃው / የወንድሞችን ምባቸውን ተቀበል) አኃው=ወንድም ፤ አኃት = እህት
  • ተዋነየ

    ተጫወተ ፤ ተነጋጋረ (ንትዋነይ/እንጨዋወት)
  • ተዛወገ

    ተዛመደ፣ እኩል ሆነ
  • ተፈሥሐ

    ትርጉም፦ ተደሰተ