መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ሰ-ስእነ

    ደከመ ፤ ታከተ
  • ሰ-ስዕነ

    አቃተ፤ተሳነ (አርዳኢሁ ይቤልዎ ለእግዚአ ኢየሱስ በእንተ ምንት ንሕነ ስዕነ አውፅኦቶ/ሐዋርያቱም ጌታችን ኢየሱስን እንዲህ አሉት "ስለምን እኛ ማስወጣት ተሳነን")
  • ሰ-ሶበ

    ጊዜ (ሶበ ይመጽእ/በሚመጣበት ጊዜ)
  • ሰረቀ

    ወሰደ ፤ አጠፋ ፤ አበላሸ
  • ሰንአ

    ገጠመ ፤ ለካ ፤ አስማማ (ተሰነአውክሙኑ ንዛዋዕ በእንተ ቤተ ክርስቲያን?)
  • ሰከየ

    ከሰሰ
  • ሰወጠ

    ተለወጠ