በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል (ሖ) ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።
-
መ-ሙቃስ
ወቀሳ -
መ-ሚ
ማ ፤ ማን ፤ ምን ፤ ምንኛ ፤ ምን ያህል (ሚ የዐቢ አምላⷈ/አምላኬ ከአንተ ማን ይበልጣል ፤ ሚ ትሤኒ እንተ ወለደታ ሐና/ ሐና የወለደቻት ምን(ኛ) ታምር -
መ-ምስለ
ጋር አብሮ (ይመጽእ እግዚእ ፡ ምስለ መላእክቲሁ/ጌታ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል) -
መ-ምዕረ
አንድ ጊዜ (ምዕረ በዘባነኪ ወምዕረ በገቦኪ ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕጻን ደከምኪ) -
መሠጠ
ነጠቀ ፤ አምሠጠ(አመለጠ) ፤ መሣጢ (ዘራፊ) -
መነነ
ናቀ (ምኑን ዮሴፍ ትሠመ / የተናቀ ዮሴፍ ተሾመ) -
መኑ
ማን - እለ መኑ አንትሙ (እነ ማን ናችሁ) መኑመ - ማን ይሆን?! -
መንገለ
ወደ/towards -
መከረ
፩. መከር ፪. ሞከረ -
መጽንሕ
መቆያ -
መጽአ
ትርጉም፡ መጣ ዐረፍተ ነገር፡ አቡየ መጽአ እምሐገሮሙ (አባቴ ከሐገሩ መጣ) ልብ በል፡ አቡየ ማለት አባቴ ማለት ነው። “እም” ማለት “ከ” ማለት ነው - ከሐገሩ እንደማለት