መዝገበ ቃላት

በዚህ ገጽ ላይ የግዕዝ ቃላት ከትርጉማቸው ያገኛሉ። ቃላትን በግእዝ ፊደላት ብቻ መድቦ ለማስቀመጥ ሲባል የመጀመርያ ፊደላቸው ከግእዝ ውጭ የሆኑ ቃላትን ከመጀመርያቸው ላይ የግእዝ ፊደል እና የሰረዝ (dash – ) ምልክት ተቀምጧል። ለምሳሌ ሖረ የሚለው ቃል በሳብዕ ፊደል () ስለሚጀምር ከመጀመርያው ሐ- በመጨመር እንደዚህ ተቀምጧል፤ ሐ-ሖረ። ይህም ለአቀማመጥ እንዲመች እንጅ ሐ- በ ሖረ ውስጥ ያለ ፊደል አይደለም። አንባቢዎች ሰረዝ እና ከዚያ በፊት ያለውን ፊደል በመዝለል ቃላትን እንዲያነቡ።

  • ለ-ሊተ

    ለኔ ፤ እኔ ፤ እኔን ፤ ወደኔ ፤ -ልኝ(ብእሲት እንተ ጸሐፈት ሊተ ጦማረ/ደብዳቤ የጻፈችልኝ ሴት ፤ ዝ ቤት ሊተ ውእቱ ዘወሀበኒ አቡየ/ይህ ቤት አባቴ የሰጠኝ ነው ፤ ስምዑኒ ሊተ/እኔን ስሙኝ)። በ፲ መራሕያን፦ ሊተ/ለነ/ለከ/ለኪ/ለክሙ/ለክን/ሎቱ/ላቲ/ሎሙ/ሎን
  • ለሐመ

    ጸና፣ በረታ፣ ከፋ
  • ለምንት

    ለምንት - ለምን ምንት - ምን
  • ለበወ

    ልብ አደረገ አስተዋለ ዐወቀ ኢለበውኩ=አልገባኝም
  • ለፌ ወለፌ

    ወዲህ ወዲያ (ኢትበሉ ለፌ ወለፌ)