በቀን 20 ደቂቃ ለግእዝ ትምህርት!!!

ግእዝን እንደማንኛውም መግባቢያ ቋንቋ - በግእዝ ቤተሰብ ለግእዝ ቤተሰብ - በኅብረት እንማራለን - በጋራ ግእዝ ቋንቋችንን እናውቃለን - Join Geez Family Today

  • መስማት
  • ማንበብ
  • መጻፍ
  • መናገር
የግእዝ ቋንቋ ሞያ ካለዎት በማስተማር ወይም ተማሪዎችን በሞያዎ በመርዳት ከአባቶች የተሰጠዎትን አደራ ይወጡ። ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ።
ሁሉም ባለው ሞያ የግእዝ ቋንቋን ለማሳደግ ይረባረብ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባላን።
ያግዙ
አንድ ቋንቋ አዲሱ ትውልድ የማይማረው ከሆነ የቋንቋው ባለሞያዎች ሲሞቱ ቋንቋውም አብሮአቸው ይሞታል
"ግእዝ ከሞቱ 240 ቋንቋዎች ውስጥ ነው" theGuardian. ቋንቋውን መታደግ የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው
Course
የግእዝ ቋንቋን መማር የቤተክርስቲያንን ሚስጢራት የምናውቅበት መስኮት ይከፍታል።
የቤተ ክርስቲያንን ቋንቋ መማር ማንም የማይቀማን በጎ ምርጫ ነው። ይማሩ!!!
Course
በቀን 20 ደቂቃ ብቻ!!! በግእዝ የማንበብ ፡ የመስማት ፡ የመጻፍ እና የመናገር ችሎታዎ ላይ ልዩነት ይፈጥራል።
አዎ ይቻላል!!! በቀን 20 ደቂቃ ብቻ!!! በተመቸዎት ቦታ እና ጊዜ ይማሩ!!! ይመዝገቡ
ይመዝገቡ

ስለ ግእዝ ቤተሰብ

This is Title

በአገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያየ ክፍለ አለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ግእዝ እንዲያንሰራራ እና መደበኛ የመግባብያ ቋንቋ እንዲሆን በመማርም ሆነ በማስተማር ከምን ጊዜውም በላይ ከፍተኛ መነቃቃ አለ። ይህ website ይህን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላት የቋንቋው ተቆርቋሪዎች የሚማማሩበት እንዲሁም የቋንቋው ባለሞያዎች የሚያስተምሩበት እና ተማሪዎችን የሚያግዙበት ነው።

ፌስቡክ ገጻችንን ይጎብኙ

Image

በሚመችዎት ጊዜ እና ቦታ online ይማሩ

ዘመኑ ያፈራውን technology እና የማህበራዊ ደኅረ ገጽ ለግእዝ ቋንቋ ትምህርት በመጠቀም ከቤትዎ እንዲሁም ከማንኛውም ቦታ ፤ በማንኛውም ሰአት በመማር ቋንቋውን ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ይጠቀሙ ፤ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ በተሻለ ያድምጡ ፤ የቤተ ክርስቲያንን ሚስጢራት ይመርምሩ

በተግባር ይማሩ

የሚማሩትን ትመህርት በተግባር ይለማመዳሉ ፤ የቋንቋው መደበኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አጋዥ መልመጃዎችን በበቂ ሁኔታ እንሰጣለን

ከሌሎች ጋር ይማሩ

የቋንቋ ትምህርት ክሂሎት/skill ስለሆነ ብቻዎን መጽሃፍ በማንበብ ወይም ቪደዮ በመመልከት ብቻ ቋንቋውን ማዳበር አይችሉም። ከእርስዎ ጋር ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር online/በስልክ እየተገናኙ የተማሩትን ይለማመዳሉ

ግእዝ በማንኛውም የእውቀት ደርጃ ላሉ

በራስዎ ፍጥነት እና የእውቀት ደረጃ ይማራሉ። 

ግእዝን እንደ ቋንቋ ለመማር ቋንቋ ፤ ጾታ አይወስነውም። በቀን 20 ደቂቃ መስጠት ብቻ!!!

ግእዝ አገራዊ ኩራታችን ነው

"ግእዝ እንደ አንድ ቋንቋ መነጋገሪያ እስኪሆን ድረስ ወደኋላ አልልም" 

“የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ የሆነው ግእዝ ቋንቋ ዛሬ ዛሬ ክፉኛ ተዳክሞ አንዴ የሞተ ቋንቋ ነው ሲባል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመሞት ላይ ያለ ቋንቋ ነው እየተባለ የሚጠቀስ ነው። የግእዝ ቋንቋ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያለ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። ያም ሆነ ይህ የግእዝ ቋንቋ በሀገሩ ኢትዮጵያ ሞተ እንዳይባል፣ ትንሳኤ ግእዝ ያስፈልገዋል። እስራኤሎች የሞተውን የአብራይስጥ ቋንቋ እንደገና አስነስተው ዛሬ ከአለማችን የጥናትና የምርምር ቋንቋዎች መካከል አንዱ አድርገውታል።” የእኛው ግእዝስ?

"ስለ ግእዝ በግእዝ ማውራት ያልቻልኩ ቤተክርስቲያን በግእዝ ሲቀደስ ከካህናት አባቶቼ ጋር እግዚኦ ተሳሃለነ ከማለት ውጭ ምን ማለት እንደሆነ የማላውቅ ብኩን የዕውቀት መፃጉዕ ነኝ፡፡ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ዕድሜ ልኬን ኖሬአለሁ፡፡ ምናለበት አንድ ቃል ስንኳ በግእዝ መፃፍ ወይም መናገር ብችል!!! ቤተክርስቲያን በግእዝ ያልተፃፈ ታሪክና ጥበብ የላትም፡፡ መለስ ብሎ ትላንትናን ማየት ፤ ለማየት ደግሞ ማየት የሚችል ዐይን ያስፈልጋል!!! ይህንን ዐይን ለማግኘት ነው ግእዝ መማርና ማወቅ ያስፈለገው ።"